ኢያሱ 21:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓይን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ዩጣና ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ቤትሼሜሽ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር ከይሁዳና ከስምዖን ምድር ተከፍለው የተሰጡ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓይንን፣ ዩጣንና ቤትሳሚስን ከነመሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት-ሳሜስንና መሰማሪያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳንና መሰማርያዋን፥ ዮጣንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይንንና መሰምርያዋን፥ ዮጣንና መሰምርያዋን፥ ቤትሳሜስንና መሰምርያዋን፥ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። |
ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ለመውጋት ዘመተ፤ በይሁዳ በሚገኘው ቤትሼሜሽ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ጦርነት ገጠሙ፤
ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።
ልባዎት፥ ሺልሒም፥ ዓይንና፥ ሪሞን ተብለው የሚጠሩት በድምሩ ኻያ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙት ታናናሽ ከተሞችንም ሁሉ ያጠቃልላሉ።
ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው።
ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”