ኢያሱ 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አገሪቱን ለመሰለል ከእስራኤላውያን መካከል ዛሬ ማታ ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ለኢያሪኮ ንጉሥ ተነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኢያሪኮም ንጉሥ፣ “እነሆ፤ ምድሪቱን ሊሰልሉ ጥቂት እስራኤላውያን በሌሊት ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ተነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኢያሪኮም ንጉሥ፥ “እነሆ፥ ከእስራኤል ልጆች ሰላዮች ሀገራችንን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ ሲባል ወሬ ሰማ። |
በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።
ከዚህ በኋላ የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺጢም ሰፈር ሁለት ሰላዮችን ላከ፤ እነርሱም የከነዓንን ምድር በተለይም የኢያሪኮን ከተማ በምሥጢር ሰልለው እንዲመለሱ አዘዛቸው፤ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ “ረዓብ” ተብላ ወደምትጠራ ወደ አንዲት ሴትኛ ዐዳሪ ቤት ገብተው ዐደሩ።
ከዚህ በኋላ የኢያሪኮ ንጉሥ “ምድሪቱን ሊሰልሉ የመጡ ስለ ሆኑ ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጥተሽ አስረክቢ!” ብሎ ወደ ረዓብ ትእዛዝ ላከ።
ስለዚህ የዳን ሕዝብ ከነገዱ ቤተሰቦች መካከል ብርታት ያላቸውን አምስት ሰዎች መረጡ፤ ምድሪቱንም አጥንተው እንዲመለሱ መመሪያ በመስጠት ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ላኩአቸው፤ እነርሱም ኮረብታማ ወደ ሆነው ወደ ኤፍሬም አገር በደረሱ ጊዜ በሚካ ቤት አደሩ፤