Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 4:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣ እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤ በሰማይ ኀይላት፣ በምድርም ሕዝቦች ላይ፣ የወደደውን ያደርጋል፤ እጁን መከልከል የሚችል የለም፤ “ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፥ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 4:35
41 Referencias Cruzadas  

“እርሱ ራሱ ይወስናል፤ እርሱንም የሚቃወም የለም፤ እርሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።


“እግዚአብሔርን የሚክድና ሕዝቡን የሚያጠምድ ንጉሥ ሲነግሥ፥ እግዚአብሔር ዝም ቢል፥ ወይም ፊቱን ቢሰውር ማን ሊወቅሰው ይችላል?


“ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”


“አምላክ ሆይ! አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል ዐውቃለሁ፤ የአንተንም ዕቅድ ማሰናከል የሚችል የለም።


እግዚአብሔር ጠቢብና ኀያል ነው፤ ማነው እርሱን ተቋቊሞ ያልተሸነፈ?


አምላካችን በሰማይ ነው፤ እርሱ የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋል።


በሰማይና በምድር፥ በጥልቅ ባሕሮችም የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።


በዙፋኑ ላይ ሆኖ በምድር ላይ ያሉትን ሁሉ ያያል።


የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።


ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ! በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ!


ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።


ንጉሥ ሁሉን ነገር ለማድረግ ሥልጣን አለው፤ “ለምን ይህን ሠራህ?” ብሎ የሚጠይቀውስ ማን አለ?


ይሁዳ ለግብጽ ሕዝብ አስፈሪ ትሆናለች፤ የይሁዳ ስም ሲነሣ እንኳ በጣም ይሸበራሉ፤ ይህም የሚሆነው የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት መዘጋጀቱን በማወቃቸው ነው።


ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።


እኔ ከጥንት ጀምሮ አምላክ ነኝ፤ ከእጄ ማንም ማንንም አያድንም፤ እኔ ያደረግኹትን መለወጥ የሚችል የለም።”


እርሱ ያድናል ይታደግማል፤ እርሱ በሰማይና በምድር ድንቅ ነገሮችንና ተአምራትን ያደርጋል፤ እርሱ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ አድኖአል።”


ስለዚህ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የዚህ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ ብናደርግ አታጥፋን፤ አንተ የፈቀድከውን ስላደረግህ ንጹሕ ደም እንዳፈሰስን አድርገህ አትቊጠርብን!” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።


እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠውን ስጦታ ለእነርሱም ከሰጣቸው፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል የምችል እኔ ማን ነኝ!”


እንዲህም የሆነው አንተ አስቀድመህ በገዛ ኀይልህና በገዛ ፈቃድህ ያቀድከውን ለመፈጸም ነው፤


ከእግዚአብሔር የመጣ ከሆነ ግን እነርሱን ልታጠፉአቸው አትችሉም፤ እንዲያውም ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ይሆንባችኋል።” እነርሱም የገማልያልን ምክር ተቀበሉ።


ሳውልም “ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?” አለ፤ እርሱም “እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤


ታዲያ ይህን በማድረግ ጌታን እናስቀናውን? እኛ ከእርሱ ይበልጥ እንበረታለንን?


ይህም፦ “የጌታን ሐሳብ ማን ሊያውቀው ይችላል? ሊመክረውስ የሚችል ማን ነው?” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።


ሁሉን ነገር በራሱ ፈቃድ የሚሠራ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዐቀደልን መሠረት በክርስቶስ አማካይነት የእርሱ ወገኖች እንድንሆን መረጠን።


“አገሪቱን ለመሰለል ከእስራኤላውያን መካከል ዛሬ ማታ ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ለኢያሪኮ ንጉሥ ተነገረው።


ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ለዔሊ አስረዳው፤ ሰውሮ ያስቀረው ምንም ነገር አልነበረም፤ ዔሊም “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህም መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos