የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤
ኢያሱ 19:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ተምናሴራ የምትባለውን ከተማ እንደ ጌታ ትእዛዝ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኤፍሬም ተራራማ ሀገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት፥ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። |
የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤
ኤፍሬም፥ ሼኢራ ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ እርስዋም የላይኛውንና የታችኛውን ቤትሖሮን፥ እንዲሁም ዑዜንሼኢራ ተብለው የሚጠሩትን ከተማዎች አሠራች።
እስራኤላውያንም ከጋዓሽ ተራራ በስተሰሜን በኩል በምትገኘው በኮረብታማይቱ በኤፍሬም አገር የራሱ የኢያሱ ርስት በሆነችው በቲምናትሴራሕ ቀበሩት።
የራሱ ድርሻ በሆነውም ርስት ተቀበረ፤ ይህም እርሱ የተቀበረበት ምድር በኮረብታማው የኤፍሬም አገር ከጋዓሽ ተራራ በስተሰሜን የሚገኘውና “ቲምናት ሴራሕ” ተብሎ የሚጠራው ነው።