Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 24:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እስራኤላውያንም ከጋዓሽ ተራራ በስተሰሜን በኩል በምትገኘው በኮረብታማይቱ በኤፍሬም አገር የራሱ የኢያሱ ርስት በሆነችው በቲምናትሴራሕ ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው፣ ከገዓስ ተራራ በስተሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምናሴራ ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 በተራራማው በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ግዛት በተምና-ሴራ ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በተራራማው በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ዳርቻ በተምናሴራ ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 24:30
6 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት።


ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በአንድ መቶ ዐሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ።


ሚካ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ይኖር ነበር፤


ከዚያም ጒዞአቸውን በመቀጠል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ሚካ ቤት መጡ።


የራሱ ድርሻ በሆነውም ርስት ተቀበረ፤ ይህም እርሱ የተቀበረበት ምድር በኮረብታማው የኤፍሬም አገር ከጋዓሽ ተራራ በስተሰሜን የሚገኘውና “ቲምናት ሴራሕ” ተብሎ የሚጠራው ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos