ኢያሱ 19:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሜያርቆን፥ ራቆንና እንዲሁም በኢዮጴ ዙሪያ ያለውን ግዛት ጭምር ያጠቃልላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜያርቆንና በኢዮጴ ፊት ለፊት ያለው ርቆን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሜያ-ርቆንን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆንን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕር በኩል በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያራቆን። |
እኛም የምትፈልገውን ግንድ ሁሉ ከሊባኖስ ተራራዎች ቈርጠን አንድ ላይ በማሰር በባሕር ላይ ተንሳፍፎ እስከ ኢዮጴ እንዲደርስ እናደርጋለን፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ልትወስደው ትችላለህ።”
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።
በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አንዲት አማኝ ነበረች፤ የስሟም ትርጒም በግሪክኛ ዶርቃ ትርጒሙም ሚዳቋ ማለት ነው፤ እርስዋ መልካም ነገር ማድረግና ለድኾች መለገሥ የምታዘወትር ሴት ነበረች፤
ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች በኢዮጴ ያሉት ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በልዳ መኖሩን ሰምተው “እባክህን ሳትዘገይ በቶሎ ድረስልን” ብለው ሁለት ሰዎች ላኩበት።
የዳንም ሕዝብ ይህን ምድር ለመውረስ የማይቻል ሆኖ ባገኙት ጊዜ ወደ ላዪሽ ሄደው አደጋ በመጣል ከተማይቱን ያዙ፤ ሕዝብዋንም ፈጅተው የራሳቸው ይዞታ አደረጉአት፤ በዚያም ሰፈሩ፤ ላዪሽ ትባል የነበረችውን ከተማ ስሟን ለውጠው በቀድሞ አባታቸው ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤