እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ቤተሰቦች ዩትራውያን፥ ፑታውያን፥ ሹማታውያንና ሚሽራዓውያን ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ ከእነርሱም የጾርዓና የኤሽታኦል ትውልድ ተገኙ።
ኢያሱ 19:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድሩም ክልል ጾርዓን፥ ኤሽታኦልን፥ ዒርሼሜሽን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወረሱትም ምድር የሚከተሉትን ያካትታል፤ ጾርዓ፣ ኤሽታኦል፣ ዒርሼሜሽ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የርስታቸውም ግዛት የሚያጠቃልለው፤ ጾርዓን፥ ኤሽታኦልን፥ ዒር-ሼሜሽን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ሠራሕት፥ አሳ፥ የሰመውስ ከተማ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፥ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥ |
እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ቤተሰቦች ዩትራውያን፥ ፑታውያን፥ ሹማታውያንና ሚሽራዓውያን ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ ከእነርሱም የጾርዓና የኤሽታኦል ትውልድ ተገኙ።
በዚያን ዘመን ጾርዓ በምትባል ከተማ የሚኖር ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከዳን ነገድ ነበር፤ ሚስቱ መኻን ስለ ነበረች ልጆች አልወለደችም፤
ወንድሞቹና የቀሩት ቤተሰቡ ሁሉ መጥተው አስከሬኑን ወሰዱት፤ ወስደውም በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል በሚገኘው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ቀበሩት፤ ሶምሶን ኻያ ዓመት ሙሉ እስራኤልን መራ።
ስለዚህ የዳን ሕዝብ ከነገዱ ቤተሰቦች መካከል ብርታት ያላቸውን አምስት ሰዎች መረጡ፤ ምድሪቱንም አጥንተው እንዲመለሱ መመሪያ በመስጠት ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ላኩአቸው፤ እነርሱም ኮረብታማ ወደ ሆነው ወደ ኤፍሬም አገር በደረሱ ጊዜ በሚካ ቤት አደሩ፤