በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፦ የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፥ እንዲሁም በቤትሻን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ፥ በጻርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፥ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅመዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤
ኢያሱ 19:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩም ከዚያ በመነሣት ከዳባሼትና በዮቅነዓም ምዕራብ ከሚገኘው ወንዝ እየተዋሰነ በምሥራቅ በኩል እስከ ማርዕላ ይደርሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ምዕራብም በመሄድ በመርዓላ በኩል ያልፋል፤ ደባሼትን ተጠግቶም በዮቅንዓም አጠገብ እስካለው ወንዝ ድረስ ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ ማራጌላ ይወጣል፤ እስከ ቤተ ራባም ይደርሳል፤ በኢያቃንም ፊት ለፊት ወዳለው ሸለቆም ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፥ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ፥ |
በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፦ የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፥ እንዲሁም በቤትሻን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ፥ በጻርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፥ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅመዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤