ኢያሱ 18:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩ በቤትሆግላ ጐን ያልፋል፤ ከጨው ባሕር በስተሰሜን እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ደቡብ ድረስ ይሄዳል። ይህም የደቡቡ ድንበር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሜናዊውን የቤትሖግላንን ተረተር ዐልፎ ይሄድና በስተ ደቡብ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚገባበት እስከ ጨው ባሕር ወሽመጥ ይዘልቃል፤ ይህም ደቡባዊ ድንበሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፤ የድንበሩም መጨረሻ በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፤ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድንበራቸውም ፍጻሜ በሰሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደርሳል፤ በደቡብም በኩል ድንበራቸው ዮርዳኖስ ነው። ይህም በደቡብ በኩል ያለው ድንበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፥ መውጫውም በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፥ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። |
እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል።
የደቡብ ድንበር ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምን ጠረፍ እያዋሰነ ያልፋል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ በኩል የሚጀምረው ከሙት ባሕር በስተ ደቡብ ጫፍ ላይ ነው።
በስተ ምዕራብ በኩል ያለው ግዛታቸው አራባን ዮርዳኖስንና በአካባቢው ያለውን ምድር ያጠቃልላል፤ በስተምሥራቅ በኩል ከገሊላ ባሕር በፒስጋ ተራራ ግርጌ እስካለው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ይደርሳል።
እርሱም በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ሸለቆ የገሊላ ባሕር ድረስ፥ በቤት የሺሞት አቅጣጫ እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ ከጨው ባሕር ወደ ደቡብ እስከ ፒስጋ ተራራ ታች ድረስ ያለውን ያጠቃልላል።
ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።