ኢያሱ 18:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ነገድ የርስት ድርሻ በየወገናቸው ወጣ፤ ለእነርሱም የተመደበላቸው ርስት የሚገኘው በይሁዳና በዮሴፍ ነገዶች መካከል ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለብንያም ነገድ የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ። በዕጣ የደረሳቸውም ምድር የሚገኘው በይሁዳና በዮሴፍ ነገዶች ርስት መካከል ሲሆን እንደሚከተለው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የዕጣቸውም ግዛት በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው በቅድሚያ ወጣ፤ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፥ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ። |
በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።
“እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባቸው ከሰጠህ ከተሞች በአንደኛዋ ውስጥ አንዳንድ ወራዶች ሰዎች ከመካከልህ ተነሥተው ነዋሪዎቹን ወደማታውቃቸው ወደ ሌሎች አማልክት ‘እንሂድና እናምልክ’ ብለው ወደ ጥፋት መንገድ መርተው መውሰዳቸውን ትሰማ ይሆናል፤
በሰሜን በኩል የሚገኘውም ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ወንዝ ተነሥቶ ወደ ኢያሪኮ ሰሜን ሽቅብ ይወጣና በምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው ኮረብታማ አገር በኩል እስከ ቤትአዌን በረሓ ይደርሳል፤