ኢያሱ 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቶች ዘሮቹ እንደ ወንዶች ዘሮቹ የርስት ድርሻ ስለ ተቀበሉ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ዘሮች ተሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናሴ ነገድ ሴት ልጆች ከወንዶቹ ጋራ ርስት ተካፍለዋልና። የገለዓድ ምድር ግን ለቀሩት የምናሴ ዘሮች ተሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ስለወረሱ፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ስለሆነ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ተቀብለዋልና፤ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆች መካከል ርስት ተቀብለዋልና፥ የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች ሆኖአልና። |
ግዛታቸውም ማሕናይምንና ባሳንን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ይህም ባሳን መላውን የባሳን ንጉሥ የዖግን ግዛት እንዲሁም በባሳን በተለይ ያኢር ተብላ በምትጠራው ስፍራ የሚገኙትን ሥልሳ ከተሞች ሁሉ ይጨምራል፤
እንዲሁም የገለዓድ እኩሌታ፥ አስታሮት እና ኤድራይ እነርሱም በባሳን የንጉሥ ዖግ ከተሞች የነበሩት ይህም ከምናሴ ነገድ ለእኩሌቶቹ የማኪር ልጆች እንደየወገናቸው ተከፋፈሉት።
የምናሴ የርስት ይዞታ ከአሴር ተነሥቶ በሴኬም በስተ ምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ሚክመታት ይደርስ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በማለፍ የዔንታፑዓሕን ሕዝብ ይጨምራል፤
ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሙሴ ርስት በባሳን ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለእኩሌቶቹ ደግሞ በዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል ከወንድሞቻቸው ጋር ኢያሱ መሬት ሰጣቸው፤ ኢያሱም ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤