ይህችው ሴት ዘግየት ብላ ሌሎች ሁለት ወንዶች ልጆችን እነርሱም የማድማናን አባት ሳፋንና የማክቢናና የጊብዓን አባት ሻዋን ወለደችለት። ካሌብ በተጨማሪ ዓክሳ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው።
ኢያሱ 15:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካሌብም፥ “ቂርያትሴፌርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” ብሎ ተናገረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካሌብ፣ “ቂርያትሤፍርን ወግቶ ለሚይዝ ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካሌብም፦ “ቂርያትሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካሌብም፥ “ሀገረ መጻሕፍትን ለሚመታ፥ ለሚይዛትም ልጄን አክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካሌብም፦ ቂርያትሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ። |
ይህችው ሴት ዘግየት ብላ ሌሎች ሁለት ወንዶች ልጆችን እነርሱም የማድማናን አባት ሳፋንና የማክቢናና የጊብዓን አባት ሻዋን ወለደችለት። ካሌብ በተጨማሪ ዓክሳ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው።
እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸውም እንዲህ ይባባሉ ነበር፤ “ይህ በየቀኑ እስራኤልን ለመፈታተን የሚወጣውን ሰው ታያላችሁን? ንጉሥ ሳኦል እርሱን ለሚገድልለት ሰው ብዙ ሀብት ለመስጠት ቃል ገብቶአል፤ ሴት ልጁንም እንደሚድርለትና የአባቱም ቤተሰብ ከግብር ነጻ እንደሚያደርግለት ተናግሮአል።”