Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አዶኒቤዜቅም ከፊታቸው ሸሸ፤ እነርሱ ግን አባረው ከያዙት በኋላ የእጆቹንና የእግሮቹን አውራ ጣቶች ቈረጡ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አዶኒቤዜቅም ከዚያ ሸሸ፤ እነርሱ ግን አሳድደው ያዙት፤ የእጆቹንና የእግሮቹንም አውራ ጣቶች ቈረጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አዶኒቤዜቅም ሸሸ፤ እነርሱ ግን አሳደው ያዙት፤ የእጆቹንና የእግሮቹንም አውራ ጣቶች ቈረጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም ሸሸ፤ ተከ​ታ​ት​ለ​ውም ያዙት፤ የእ​ጁ​ንና የእ​ግ​ሩ​ንም አውራ ጣቶች ቈረጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አዶኒቤዜቅም ሸሸ፥ አሳድደውም ያዙት፥ የእጁንና የእግሩንም አውራ ጣት ቈረጡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 1:6
12 Referencias Cruzadas  

ይህም ንጉሣዊ ትእዛዝ አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛ ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን፥ ማለትም አይሁድ እንዲገደሉ በታቀደበት ዕለት በመላው የፋርስ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሁሉ ሥራ ላይ እንዲውል ተወሰነ።


እግዚአብሔር ልዑላኑን አዋረደ፤ በምድረ በዳም አሸዋ ውስጥ እንዲንከራተቱ አደረገ።


ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት ለመያዝ፥ መኳንንቶቻቸውን በእግር ብረት ለማሰር፥


መከታችን እግዚአብሔር ሆይ! ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤ ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ውሃውም በግብጻውያን፥ በሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ይመለስባቸው” አለው።


በዐይን ምትክ ዐይን፥ በጥርስ ምትክ ጥርስ፥ በእጅ ምትክ እጅ፥ በእግር ምትክ እግር፥


እርሱንም ዕረድና ከደሙ ጥቂት ወስደህ የአሮንንና የልጆቹን ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ትቀባለህ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ርጨው።


እነሆ እኔ እግዚአብሔር እናንተንም የምላችሁ ይህ ነው፦ ‘አልታዘዛችሁም፤ ወገኖቻችሁ ለሆኑ እስራኤላውያንም ነጻነት አልሰጣችሁም፤’ ስለዚህም እኔ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ ትሞቱ ዘንድ እተዋችኋለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገውም ነገር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ።


በከተማይቱ ዙሪያ በማቅራራት ደንፉ! እነሆ ባቢሎን እጅዋን ሰጥታለች፤ ግንቦችዋ ተጥሰዋል፤ ቅጽሮችዋም ፈራርሰዋል፤ ባቢሎናውያንን እበቀላለሁ፤ እናንተም ተበቀሉአቸው፤ በሌሎች ላይ የፈጸሙትን ጭካኔ በእነርሱም ላይ ፈጽሙባቸው፤


ካሌብም፥ “ቂርያትሴፌርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” ብሎ ተናገረ፤


በዚያም አዶኒቤዜቅን በቤዜቅ አግኝተው ከእርሱ ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ከነዓናውያንንና ፈሩዛውያንን ድል አደረጉአቸው።


አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos