ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ።
ኢያሱ 15:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከበኣላ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ሴይር ይታጠፍና ክሳሎን ተብሎ በሚጠራው በይዓሪም ኰረብታ ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ ቍልቍል ወደ ቤትሳሚስ በመውረድ ወደ ተምና ይሻገራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፥ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ቤትሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ። |
ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ።
አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቈጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤
በዚሁ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በደቡባዊ ይሁዳ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽ፥ አያሎን፥ ገዴሮት፥ ሶኮ፥ ቲምናና ጊምዞ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች በድል አድራጊነት ያዙ፤ በዚያም ኖሩ።
ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤
ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤትዐናትና ቤትሼሜሽ ተብለው የሚጠሩ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች በዙሪያቸው ታናናሽ ከተሞች ጋር በዚህ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፤
ዓይን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ዩጣና ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ቤትሼሜሽ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር ከይሁዳና ከስምዖን ምድር ተከፍለው የተሰጡ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው።
ከዚህ በኋላ ሶምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም በወይን ተክል ውስጥ አልፈው ሲሄዱ አንድ ደቦል አንበሳ እያገሣ መጣበት፤
ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”