በያዕቆብ ልጆች ላይ ምንም ዐይነት ጥንቈላ፥ በእስራኤልም ላይ ምንም ዐይነት አስማት አይሠራም፤ እነሆ፥ አሁን ለያዕቆብና ለእስራኤል፥ ‘እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ተመልከቱ!’ ይባላል።
ኢያሱ 13:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ከገደሉአቸውም መካከል አንዱ ጠንቋይ እየተባለ ይጠራ የነበረው የቢዖር ልጅ በለዓም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጦር ሜዳ ከሞቱት ሌላ እስራኤላውያን የቢዖርን ልጅ ሟርተኛውን በለዓምን በሰይፍ መትተው ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር የእስራኤል ልጆች ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሟርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በአንድነት በሰይፍ ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር የእስራኤል ልጆች ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉት። |
በያዕቆብ ልጆች ላይ ምንም ዐይነት ጥንቈላ፥ በእስራኤልም ላይ ምንም ዐይነት አስማት አይሠራም፤ እነሆ፥ አሁን ለያዕቆብና ለእስራኤል፥ ‘እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ተመልከቱ!’ ይባላል።
በለዓምም እነሆ፥ እስራኤልን መመረቅ እግዚአብሔርን እንዳስደሰተው ስለ ተረዳ ከዚህ በፊት እንዳደረገው የሟርት ምልክት መከተል አላስፈለገውም፤ ፊቱንም ወደ በረሓው መለሰ።
በመጨረሻም በለዓም ባላቅን “እነሆ፥ እኔ ወደ ራሴ ሕዝብ ተመልሼ መሄዴ ነው፤ ነገር ግን ከመሄዴ በፊት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ፊት በሕዝብህ ላይ የሚያደርጉትን በመግለጥ ላስጠነቅቅህ እወዳለሁ” ካለው በኋላ፥
በምዕራብ በኩል የዮርዳኖስም ወንዝ ለሮቤል ነገድ የርስቱ ወሰን ነበር፤ እንግዲህ ለሮቤል ነገድ ቤተሰቦች ርስት ሆነው የተሰጡአቸው ከተሞችና መንደሮች እነዚህ ነበሩ።
እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ነገር ግን የምነቅፍብህ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ፤ ይኸውም የበለዓምን ትምህርት የያዙ አንዳንድ ሰዎች በመካከላችሁ አሉ፤ ይህ በለዓም የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ በመብላትና ዝሙት በማድረግ እንዲሰናከሉ ባላቅን የመከረ ነው።