ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
ኢያሱ 10:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢያሱና ሠራዊቱ ከዔግሎን ወጥተው በኬብሮን ላይ አደጋ ጣሉባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከዔግሎን ወደ ኬብሮን ወጡ፤ ወጓትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከዔግሎም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከአዶላም ወደ ኬብሮን ወጡ፤ ወጉአትም፤ ያዙአትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኦዶላም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥ ያዙአትም፥ |
ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
ዳዊት በኬብሮን ሳለ ብዙ የሠለጠኑ ወታደሮች ወደ እርሱ ሠራዊት ገቡ፤ እግዚአብሔር በሰጠውም የተስፋ ቃል መሠረት በሳኦል እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ብዙ ርዳታ አደረጉለት፤ ቊጥራቸውም እንደሚከተለው ነበር፦ ከይሁዳ ነገድ፦ ጋሻና ጦር በሚገባ የታጠቁ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ወታደሮች፥ ከስምዖን ነገድ፦ በሚገባ የሠለጠኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ወታደሮች፥ ከሌዊ ነገድ፦ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት የዮዳሄ ተከታዮች ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ታዋቂ ጦረኛ ከሆነው ከጻዶቅ ዘመዶች፦ ኻያ ሁለት የጦር አዛዦች፥ የሳኦል ወገን ከሆነው ከብንያም ነገድ፦ ሦስት ሺህ ሰዎች፤ ይሁን እንጂ ከብንያም ነገድ አብዛኛው ሕዝብ ለሳኦል ያላቸውን ታማኝነት እንደ ቀጠሉ ነበሩ። ከኤፍሬም ነገድ፦ ኻያ ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሆኑ፥ ሁሉም በየጐሣቸው ዝነኞች የሆኑ ጀግኖች ነበሩ። በምዕራብ በኩል ካለው ከምናሴ ነገድ፦ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ሲሆኑ፥ እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በተለይ የተመረጡ ናቸው። ከይሳኮር ነገድ፦ ሁለት መቶ መሪዎች ሲሆኑ፥ በእነርሱ አመራር ሥር ያሉትንም ያጠቃልላል፤ እነዚህ መሪዎች እስራኤል ምን ማድረግና መቼ ማድረግ እንደሚገባት የሚያውቁ ናቸው። ከዛብሎን ነገድ፦ እምነት የሚጣልባቸው ለጦርነት ዝግጁዎች የሆኑ በማንኛውም መሣሪያ መጠቀም የሚችሉ ኀምሳ ሺህ ወታደሮች፤ ከንፍታሌም ነገድ፦ አንድ ሺህ የጦር መሪዎችና ጋሻና ጦር ያነገቡ ሠላሳ ሰባት ሺህ ወታደሮች ነበሩ። ከዳን ነገድ፦ ኻያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ የሠለጠኑ ወታደሮች ነበሩ። ከአሴር ነገድ፦ አርባ ሺህ ለጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች ነበሩ። ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ካሉት ከሮቤል፥ ከጋድና ከምናሴ ነገዶች፦ በማንኛውም ዐይነት መሣሪያ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው አንድ መቶ ኻያ ሺህ ወታደሮች ነበሩ።
በመጀመሪያው ወደ ኔጌብ ሄደው ወደ ኬብሮን መጡ፤ ይህችም ኬብሮን “ዐናቂም” ተብለው የሚጠሩ የግዙፋን ሰዎች ዘር የሆኑ አሒማን፥ ሼሻይ እና ታልማይ የሚባሉት ጐሣዎች መኖሪያ ነበረች። (ኬብሮን የተመሠረተችውም በግብጽ ምድር ጾዓን ተብላ የምትጠራው ከተማ ከመቈርቈርዋ ሰባት ዓመት ቀደም ብሎ ነበር።)
ስለዚህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሆሃም ተብሎ ለሚጠራው ለኬብሮን ንጉሥ፥ ፒራም ለተባለው ለያርሙት ንጉሥ፥ ያፊዓ ለተባለው ለላኪሽ ንጉሥና ደቢር ለተባለው ለዔግሎን ንጉሥ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦
እርስዋንም ይዘው ንጉሡን፥ በከተማይቱና በአካባቢዋም የገጠር ከተሞች ያገኙትን ሁሉ ገደሉ፤ ኢያሱም ልክ በዔግሎን ባደረገው ዐይነት ከተማይቱ እንድትደመሰስ ፈረደባት፤ በእርስዋም ውስጥ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም።
እነዚህ የኢየሩሳሌም፥ የኬብሮን፥ የያርሙት፥ የላኪሽና የዔግሎን ገዢዎች አምስቱ አሞራውያን ነገሥታት ሠራዊታቸውን አስተባብረው፥ የጦር ግንባር በመፍጠር፥ ገባዖንን ከበው አደጋ ጣሉባት።
እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ከይሁዳ ነገድ ኪርያት ዐርባን ወይም ኬብሮን እርስት አድርጎ ሰጠው። (አርባ የዐናቅ አባት ነበር)
ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ ከሆነችው ኬብሮን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር በተጨማሪ ለካህኑ ለአሮን ዘሮች ከዚህ የሚከተሉት ከተሞች ተመደቡላቸው፤ እነርሱም ሊብና፥ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥
የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀድሞ ኪርያት አርባዕ ትባል ነበር፤ እነርሱም የሼሻይን፥ የአሒማንንና የታልማይን ጐሣዎች አሸነፉ።