“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
ዮናስ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በማግስቱ ጠዋት እግዚአብሔር አንድ ትል አዘጋጀ፤ ትልዋም ቅሊቱን በላች፤ እርሷም ደረቀች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን በማለዳ እግዚአብሔር ትል አመጣ፤ ትሉም ቅሉን በላ፤ ቅሉም ደረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱ ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርሷም የጉሎውን ተክል መታች፤ ደረቀም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘዘ፤ እርስዋም ቅሊቱን መታቻት፤ ደረቀችም። |
“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል።
ጥላ በማግኘት ከፀሐይ ግለት እንዲድን እግዚአብሔር አምላክ አንድ የቅል ተክል አብቅሎ ቅጠሎችዋ ከዮናስ ራስ በላይ እንዲሆኑ አደረገ፤ ዮናስም ከቅሉ ሐረግ ጥላ በማግኘቱ እጅግ ተደሰተ።