La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮናስ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕር መሠረት ጣልከኝ፤ በዙሪያዬም ውሃ ከበበኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ላይ አለፉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጥልቅ ወደ ሆነው፣ ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤ ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣ በላዬ ዐለፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም አለ፦ “በመከራዬ ሆኜ ጌታን ጠራሁት፥ እርሱም መለሰልኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም ሰማህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“በመ​ከ​ራዬ ሳለሁ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ በሲ​ኦ​ልም ሆድ ውስጥ የጩ​ኸ​ቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌ​ንም አዳ​መ​ጥህ።

Ver Capítulo



ዮናስ 2:3
11 Referencias Cruzadas  

የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፤


ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ።


እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።


መከራ በደረሰብኝ ጊዜ፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ፤ እርሱም ሰማኝ።


በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል፤ ማዕበልህና ሞገድህ በእኔ ላይ አለፈ።


ውሃ ከእራሴ በላይ ሞልቶ ሲፈስ የምሞትበት ጊዜ የተቃረበ መሰለኝ።


“እግዚአብሔር ሆይ! በጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆኜ፥ ስምህን ጠራሁ።