ዮሐንስ 9:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ኢየሱስ የተባለ ሰው ጭቃ ለውሶ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ፤ እኔም ሄጄ ታጠብኩና ለማየት ቻልኩ” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ኢየሱስ የሚሉት ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኔን ቀባኝ፤ ወደ ሰሊሆም ሄጄ እንድታጠብም ነገረኝ፤ ሄጄ ታጠብሁ፤ ማየትም ቻልሁ” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ መልሶ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ፤’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ፥ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው በምራቁ ጭቃ አድርጎ ዐይኖችን ቀባኝና ሂደህ በሰሊሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠብሁና አየሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ መልሶ፦ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ አይኖቼን ቀባና፦ ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ” አለ። |
በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው ስለሞቱት ዐሥራ ስምንት ሰዎች ምን ታስባላችሁ? እነርሱ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የባሱ ኃጢአተኞች የነበሩ ይመስሉአችኋልን?
እርሱም “አስቀድሜ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን መስማት አልፈለጋችሁም፤ ታዲያ፥ ስለምን እንደገና መስማት ትፈልጋላችሁ? እናንተም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆን ትፈልጋላችሁን?” አላቸው።