ዮሐንስ 7:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ እንጂ የሰውን ፊት አይታችሁ በማዳላት አትፍረዱ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውን ፊት በማየት መፍረድ ትታችሁ ቅን ፍርድ ፍረዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእውነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ ለሰው ፊት በማድላት አትፍረዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።” |
“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።
“እኔ የሠራዊት አምላክ ለሕዝቤ የሰጠሁት ትእዛዝ ይህ ነበር፤ ‘በትክክል ፍረዱ፥ እርስ በርሳችሁም አንዳችሁ ለሌላው ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤
እናንተ የምትመለከቱት በውጪ የሚታየውን ነገር ብቻ ነው፤ ማንም ሰው የክርስቶስ ነኝ ብሎ ቢተማመን እንደገና ያስብበት፤ እኛም እንደ እርሱ የክርስቶስ መሆናችንን ይገንዘብ።