ዮሐንስ 7:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አይሁድም፥ “ይህ ሰው ሳይማር ይህን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ቻለ?” እያሉ ይደነቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም በመደነቅ፣ “ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ሊያውቅ ቻለ?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል?” ብለው ይደነቁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “ይህ ሳይማር መጽሐፍን እንዴት ያውቃል?” እያሉ ትምህርቱን አደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድም፦ “ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል?” ብለው ይደነቁ ነበር። |
ወደ አገሩ ወደ ናዝሬት ከተማ መጥቶ በምኲራቦቻቸው ሕዝብን ያስተምር ነበር፤ የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና ይህን ድንቅ ሥራ ከወዴት አመጣው?
የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤
ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት መናገራቸውን የሸንጎ አባሎች ባዩ ጊዜ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ያውቁ ስለ ነበረ ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ዐወቁ፤
ከዚያ በፊት እርሱን የሚያውቁትም ሰዎች ይህን ሲያደርግ በተመለከቱ ጊዜ “የቂስን ልጅ ምን ነካው? ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።