ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን ይህን አይተው፦ “ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር አብሮ ይበላል” እያሉ በኢየሱስ ላይ አጒረመረሙ።
ዮሐንስ 6:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኢየሱስ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” በማለቱ አይሁድ በእርሱ ላይ አጒረመረሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” በማለቱ ያጕረመርሙበት ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ፤” በማለቱ ማንጐራጐር ጀመሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም ስለ እርሱ አንጐራጐሩ፤ “ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” ብሎአቸዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አይሁድ፦ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና፦ |
ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን ይህን አይተው፦ “ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር አብሮ ይበላል” እያሉ በኢየሱስ ላይ አጒረመረሙ።
ፈሪሳውያንና ወገኖቻቸው የሆኑ የሕግ መምህራን “ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የምትበሉትና የምትጠጡት ስለምንድን ነው?” ብለው በኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ አጒረመረሙ።
የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤
እንግዲህ ከሰማይ የወረደው እንጀራ ይህ ነው፤ እርሱም አባቶቻችሁ እንደ በሉት ዐይነት አይደለም፤ ያን እንጀራ የበሉ ሞተዋል፤ ይህን እንጀራ የሚበሉ ግን ዘለዓለም ይኖራሉ።”
ሕዝቡም ስለ እርሱ በሹክሹክታ ይነጋገሩ ነበር፤ አንዳንዶቹ “እርሱ ደግ ሰው ነው” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ እርሱ ሕዝቡን ያስታል” ይሉ ነበር።
እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ የሚያጒረመርሙና በምንም ነገር የማይደሰቱ ናቸው፤ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው በትዕቢት ቃል የተሞላ ነው፤ የራሳቸውን ጥቅም በመፈለግ ሰውን ይለማመጣሉ።