Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 6:66 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

66 በዚህም ምክንያት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ኢየሱስን መከተል ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

66 ከዚህም በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ከዚያም ወዲያ አልተከተሉትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

66 በዚህም ምክንያት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደፊትም ከእርሱ ጋር ወደ ፊት መሄድም አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

66 ስለ​ዚ​ህም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ወደ ኋላ​ቸው የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ከዚ​ያም ወዲህ አብ​ረ​ውት አል​ሄ​ዱም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:66
17 Referencias Cruzadas  

ከእኔ የራቁትን፥ እኔን መከተል የተዉትንና ወደ እኔም መጥተው እኔ እንድመራቸው ያልጠየቁኝን አጠፋለሁ።”


ወጣቱ ግን ብዙ ሀብት ስለ ነበረው ይህን በሰማ ጊዜ እየተከዘ ሄደ።


ኢየሱስም “ለማረስ በእጁ ዕርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም፤” ሲል መለሰለት።


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሠርጉ ተጠርተው ነበር።


ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን በሰሙ ጊዜ፥ “ይህ አነጋገር ከባድ ነው፤ ማን ሊቀበለው ይችላል?” አሉ።


ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዳንዶች የማያምኑ አሉ፤” ኢየሱስ ይህን የተናገረው ከመጀመሪያ አንሥቶ የማያምኑ እነማን እንደ ነበሩና አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ስለ ነበር ነው።


ስለዚህ ወንድሞቹ ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “ደቀ መዛሙርትህ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ፤


ኢየሱስ በእርሱ ላመኑት አይሁድ እንዲህ አለ፤ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ትሆናላችሁ፤


በእስያ ያሉት ሁሉ እኔን ትተውኝ እንደ ሄዱ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም መካከል ፊጌሉስና ሄርሞጌኔስ ይገኛሉ።


ዴማስ ይህን ዓለም ወዶ ተለይቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፥ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


የእኔ የሆነ ጻድቁ ሰው ግን በእምነት ሕይወትን ያገኛል፤ ወደ ኋላው ቢያፈገፍግ ግን እኔ በእርሱ አልደሰትም።”


እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos