ከዚያም አልፈን የኤፍሬም ቅጽር በር፥ የይሻና ቅጽር በር፥ የዓሣ ቅጽር በር ተብለው ወደተሰየሙትና የሐናንኤል ግንብ የመቶዎቹ ግንብና የበጎች ቅጽር በር ተብለው ወደሚጠሩት ስፍራዎች መጣን፤ ሰልፋችንንም ያበቃነው ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ወደ ሆነው የዘበኞች ቅጽር በር ወደሚባለው ቦታ ስንደርስ ነበር።
ዮሐንስ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ የምንጭ ኲሬ ነበረ፤ በዙሪያውም አምስት ከላይ ክዳን ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም፣ በበጎች በር አጠገብ፣ ዐምስት ባለመጠለያ መመላለሻዎች የነበሯት፣ በአራማይክ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የተባለች አንዲት መጠመቂያ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። |
ከዚያም አልፈን የኤፍሬም ቅጽር በር፥ የይሻና ቅጽር በር፥ የዓሣ ቅጽር በር ተብለው ወደተሰየሙትና የሐናንኤል ግንብ የመቶዎቹ ግንብና የበጎች ቅጽር በር ተብለው ወደሚጠሩት ስፍራዎች መጣን፤ ሰልፋችንንም ያበቃነው ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ወደ ሆነው የዘበኞች ቅጽር በር ወደሚባለው ቦታ ስንደርስ ነበር።
የከተማይቱ ቅጽር እንደገና የተሠራው በዚህ ዐይነት ነበር፦ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና የእርሱ ሥራ ባልደረቦች የሆኑት ካህናት “የበጎች በር” ተብሎ የሚጠራውን ቅጽር በር እንደገና ሠርተው ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት፤ በሮችንም አበጁለት፤ ቅጽሩንም “መቶ” ተብሎ እስከሚጠራው የመጠበቂያ ግንብና “ሐናንኤል” ተብሎ እስከሚጠራው ሌላ የመጠበቂያ ግንብ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ አደረጉት።
ከጥንቱ ኲሬ የሚወርደውን ውሃ ለመመለስ በከተማይቱ ውስጥ ግድብ ሠራችሁ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ዐቅዶ ያደረገው እግዚአብሔር መሆኑ ትዝ አላላችሁም።
ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጪ አውጥቶ “ጠፍጣፋ ድንጋይ” በተባለው ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ገበታ” ይባላል።
ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ስለ ነበር፥ ከአይሁድ ብዙዎቹ ጽሑፉን አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፥ በላቲንና በግሪክ ቋንቋ ነበር።
ኢየሱስም “ማርያም!” አላት። እርስዋም ወደ እርሱ ዞር ብላ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ረቡኒ!” አለችው፤ ትርጓሜውም “መምህር ሆይ!” ማለት ነው።
እንዲናገር በፈቀደለት ጊዜ ጳውሎስ በደረጃ ላይ ቆሞ ሕዝቡ ዝም እንዲል በእጁ ጠቀሰ፤ ሕዝቡ ጸጥ ባለ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤