ዮሐንስ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፥ ሲካር ተብላ ወደምትጠራ የሰማርያ ከተማ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሰማርያ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደ ነበረች፣ ሲካር ወደምትባል ከተማ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትገኝ ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው በወይን ቦታ አቅራቢያ ወደ አለችው ሲካር ወደምትባለው የሰማርያ ከተማ ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ |
በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይና በሰማርያ ታናናሽ ከተሞች በየኮረብታው ባሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ የተናገረው የትንቢት ቃል በእርግጥ ይፈጸማል።”
በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ መንገድ ከመሄድ የተነሣ ስለ ደከመው በጒድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ።
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።