ዮሐንስ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለ ነበር ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአይሁድ ፋሲካም እንደ ተቃረበ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአይሁድም የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዚያም የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ሁሉ አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ።
ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በውስጡ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሰዎች ያስወጣ ጀመር፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ፤
እነሆ፥ ጊዜው ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በፊት ነበር፤ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት መድረሱን ዐወቀ። በዚህ በዓለም ያሉትን የራሱን ወገኖች ወዶአቸው ነበር፤ እስከ መጨረሻም ወደዳቸው።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ የፋሲካን፥ የመከርንና የዳስ በዓልን ለማክበር እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ይሰብሰቡ፤ በዓሉን ለማክበር በሚወጡበት ጊዜ ባዶ እጃቸውን አይምጡ፤