ዮሐንስ 18:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ ወደ ሐና ወሰዱት፤ ሐና በዚያ ዓመት የካህናት አለቃ ለነበረው ለቀያፋ ዐማቱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያ የቀያፋ አማት ወደ ነበረው ወደ ሐና አመጡት፤ ቀያፋም የዓመቱ ሊቀ ካህናት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀድመውም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስቀድሞም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት የካህናት አለቃ ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስቀድመውም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና። |
እርሱም ይህን የተናገረው፥ ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም፤ ነገር ግን በዚያን ዓመት እርሱ የካህናት አለቃ ስለ ነበረ፥ ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ መሞት እንደሚገባው ሲያመለክት ይህን ትንቢት ተናገረ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ አገረ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ጊዜውም ጠዋት ማለዳ ነበር፤ አይሁድ ለፋሲካ በዓል የሚታረደውን በግ መብላት ስለ ነበረባቸው እንዳይረክሱ በማለት ወደ አገረ ገዢው ግቢ ውስጥ አልገቡም።
ኢየሱስም “ከእግዚአብሔር ሥልጣን ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር፤ ሆኖም ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ የባሰ ኃጢአት አለበት” አለው።