ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ስለ ነገርኳችሁ ልባችሁ በሐዘን ተሞልቶአል።
ይህን በመናገሬም ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፤
ነገር ግን ይህን ስለ ነገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።
ነገር ግን ይህን ስለ ነገርኋችሁ በልባችሁ ኀዘን ሞላ።
ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።
ከጸሎቱ ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣ፤ ከሐዘን ብዛት የተነሣ ተኝተው አገኛቸውና እንዲህ አላቸው፤
እርሱም “በጒዞ ላይ ሳላችሁ የምትነጋገሩበት ይህ ነገር ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም እያዘኑ ቀጥ ብለው ቆሙ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤