እግዚአብሔር ሕዝቡን “እኔ እናንተን ወድጄአችኋለሁ” ይላል። እናንተ ግን “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፥ “ዔሳውና ያዕቆብ ወንድማማቾች ነበሩ፤ እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ።
ዮሐንስ 15:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድቷደዱ የእኔ ትእዛዝ ይህች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። |
እግዚአብሔር ሕዝቡን “እኔ እናንተን ወድጄአችኋለሁ” ይላል። እናንተ ግን “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፥ “ዔሳውና ያዕቆብ ወንድማማቾች ነበሩ፤ እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ።
ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።
እመቤት ሆይ፥ አሁንም ዐደራሽን፥ ይህ የምጽፍልሽ አዲስ ትእዛዝ አይምሰልሽ፤ አሁን የምጽፍልሽ “እርስ በርሳችን እንዋደድ” የሚለውን ከመጀመሪያ አንሥቶ በእኛ ዘንድ የነበረውን ትእዛዝ ነው።