ዮሐንስ 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! እንዲህስ ከሆነ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንም፥ ራሴንም እጠበኝ!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምዖን ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ እንግዲያውስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንም ራሴንም ዕጠበኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! እንግዲያውስ እግሬን ብቻ ሳይሆን፥ እጄንና ራሴንም ጭምር” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምዖን ጴጥሮስም፥ “አቤቱ፥ እንኪያስ የምታጥበኝ እጆችንና ራሴንም እንጂ እግሮችን ብቻ አይደለም፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምዖን ጴጥሮስም፦ “ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም” አለው። |
ስለዚህ ጲላጦስ ይህ ነገር ሁከት እንደሚያስነሣ እንጂ ሌላ ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ ውሃ አስመጥቶ “እኔ ለዚህ ሰው ሞት ኀላፊ አይደለሁም፤ ኀላፊነቱ የእናንተ ነው!” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
ኢየሱስም “ሰውነቱን የታጠበ ሁለመናውም ንጹሕ በመሆኑ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፤ እናንተም ንጹሖች ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁም ንጹሖች አይደላችሁም” አለው።
ስለዚህ ከክፉ ኅሊና እንድንነጻ ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፥ ቅን ልብና እውነተኛ እምነት ይዘን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።
ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድን የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤