እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”
ዮሐንስ 12:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እነሆ፥ የሰው ልጅ የሚከበርበት ሰዓት ደርሶአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የሰው ልጅ የሚከብርበት ሰዓቱ ደርሷል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁን የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ጊዜው ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ “የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል። |
እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”
የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ።
ከዚህ በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ መጣና እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም ገና ተኝታችኋልን? ዕረፍትም እያደረጋችሁ ነውን? እነሆ፥ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ የሚሰጥበት ሰዓቱ ደርሶአል፤
ሦስተኛም ጊዜ ወደ እነርሱ መጥቶ፥ እንዲህ አላቸው፦ “አሁንም ገና ተኝታችኋልን? አሁንም ዕረፍት ታደርጋላችሁን? እንግዲህስ በቃ! ሰዓቱ ደርሶአል! እነሆ! የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል።
ደቀ መዛሙርቱ ይህ ነገር በመጀመሪያ አልገባቸውም ነበር፤ ግን ኢየሱስ በክብር ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈና ለእርሱም እንደ ተደረገለት አስታወሱ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! ነፍሴ ተጨንቃለች፤ ምን ልበል? ‘አባት ሆይ! ከዚህች ሰዓት አድነኝ ልበልን?’ ይህን እንዳልል ግን እኔ የመጣሁት ለዚህች የመከራ ሰዓት ነው።
እነሆ፥ ጊዜው ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በፊት ነበር፤ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት መድረሱን ዐወቀ። በዚህ በዓለም ያሉትን የራሱን ወገኖች ወዶአቸው ነበር፤ እስከ መጨረሻም ወደዳቸው።
ይህንንም የተናገረው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ ኢየሱስ ገና ወደ ክብር ስላልወጣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር።