ዮሐንስ 11:57 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ኢየሱስን መያዝ እንዲችሉ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው ቢኖር እንዲጠቊማቸው ሰውን ሁሉ አዘው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን ይይዙት ዘንድ የት እንዳለ የሚያውቅ ሰው እንዲጠቍም ትእዛዝ ሰጥተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ እርሱ ያለበትን ስፍራ የሚያውቅ ሰው ቢኖር እንዲያመለክታቸው አዝዘው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ያለበትን የሚያውቅ ቢኖር ይይዙት ዘንድ እንዲያመለክታቸው አዘዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ እርሱ ያለበትን ስፍራ የሚያውቀው ሰው ቢኖር እንዲያመለክታቸው አዘው ነበር። |
ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሸንጎውን አባሎች ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ስለሚያደርግ ምን ብናደርግ ይሻላል?
ወላጆቹ ይህን ያሉት ኢየሱስን “መሲሕ ነው” የሚል ሰው ቢኖር የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከምኲራብ ሊያስወጡት ተስማምተው ስለ ነበረ እነርሱን በመፍራት ነበር።