ዮሐንስ 11:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ “አልዓዛር! ና ውጣ!” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ በታላቅ ድምፅ፣ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” ብሎ ተጣራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር ሆይ! ና፥ ወደ ውጭ ውጣ፤” ብሎ ጮኸ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ብሎ በታላቅ ቃል ጮኸና፥ “አልዓዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ “አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና” ብሎ ጮኸ። |
ሟቹ አልዓዛርም እጆቹና እግሮቹ በመገነዣ እንደ ተገነዙ ከመቃብሩ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር፤ ኢየሱስም “ፍቱትና ተዉት ይሂድ!” አላቸው።
የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀን ሲቀረው፥ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ ቢታንያ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሚኖርባት መንደር ነች።
በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።
ጴጥሮስም ሰዎቹን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ነገር ስለምን ትደነቃላችሁ? ስለምንስ ትኲር ብላችሁ ታዩናላችሁ? እኛ በራሳችን ኀይል ወይም በራሳችን መልካም ሥራ ይህን ሰው እንዲራመድ ያደረግነው ይመስላችኋልን?
ጴጥሮስ ግን ሁሉንም ወደ ውጪ አስወጣና ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ አስከሬኑም መለስ አለና “ጣቢታ! ተነሺ!” አለ፤ እርስዋም ዐይኖችዋን ከፈተች፤ ጴጥሮስንም አየች፤ ተነሥታም ቁጭ አለች።