Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁድ ኢየሱስ በዚያ መኖሩን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ብለው ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከአይሁድም ብዙ ሰዎች በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፤ የመጡትም በኢየሱስ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከአ​ይ​ሁ​ድም ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ እን​ዳለ በዐ​ወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመ​ጡ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለማ​የት ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣ​ዉን አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከአይሁድም ብዙ ሕዝብ በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፥ ከሙታንም ያስነሣውን አልዓዛርን ደግሞ እንዲያዩ ነበረ እንጂ ስለ ኢየሱስ ብቻ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 12:9
8 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ራሱ ‘ጌታ’ ብሎ ከጠራው ታዲያ፥ መሲሕ ለዳዊት እንዴት ልጁ ይሆናል?” ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰሙት ነበር።


የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀን ሲቀረው፥ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ ቢታንያ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሚኖርባት መንደር ነች።


የካህናት አለቆች ግን አልዓዛርንም ለመግደል ተማከሩ።


በማግስቱ ለፋሲካ በዓል የመጡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የሚመጣ መሆኑን ሰሙ።


ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ አብረውት የነበሩ ሁሉ ስለ ኢየሱስ ይመሰክሩ ነበር።


የዳነውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ በማየታቸው በእነርሱ ላይ የሚሉትን አጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos