በአራተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ “የበረከት ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔር ስላደረገላቸውም ነገር ሁሉ አመሰገኑት፤ ሸለቆው “በረከት” ተብሎ የተጠራውም ስለዚህ ነው።
ኢዩኤል 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሕዛብ ሁሉ ተነሣሥተው ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ ይሂዱ፤ እኔ እግዚአብሔር በዙሪያ ባሉት አሕዛብ ላይ ለመፍረድ እዚያ እቀመጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቦች ይነሡ፤ ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ ፈጥነው ይውረዱ፤ ዙሪያውን ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ላይ ልፈርድ፣ በዚያ እቀመጣለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሕዛብ ሁሉ ይነሡ፤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፤ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና። |
በአራተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ “የበረከት ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔር ስላደረገላቸውም ነገር ሁሉ አመሰገኑት፤ ሸለቆው “በረከት” ተብሎ የተጠራውም ስለዚህ ነው።
እርሱ በብዙ መንግሥታት መካከል በመፍረድ አለመግባባትን ያስወግዳል፤ ስለዚህም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያም በኋላ የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም።
ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ በእስራኤል ምድር በሚገኘው፥ ከሙት ባሕር በስተ ምሥራቅ ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ውስጥ፥ ለጎግ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ከብዛቱ የተነሣ መተላለፊያ መንገዱን ይዘጋል፤ ጎግና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ይቀበራሉ፤ ስለዚህም ያ ሸለቆ ‘የጎግ ሠራዊት ሸለቆ’ ተብሎ ይጠራል።
አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ የእኔ የሆኑትን ሕዝቤን እስራኤልን በሕዝቦች መካከል ስለ በታተኑና ምድሪቱን ስለ ተካፈሉ በኢዮሣፍጥ ሸለቆ ወደ ፍርድ አቀርባቸዋለሁ።
እርሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በቅርብና በሩቅ ባሉ ታላላቅ መንግሥታት መካከል ያለውን አለመግባባት ያስወግዳል፤ ስለ ሆነም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያ በኋላም የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም።
በዚያን ቀን እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማል፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በሰፊ ሸለቆ በሁለት ይከፈላል፤ ስለዚህም የተራራው እኩሌታ ወደ ሰሜን እኩሌታውም ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል።
ከዚህ በኋላ ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ፥ ነጭ ፈረስም አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ የሚባል ነው፤ እርሱ በትክክል ይፈርዳል፤ ይዋጋልም፤