ሰይፋቸውን በእጃቸው ያያዙትን ጭፍሮች ሁሉ ንጉሡን ከአደጋ ለመከላከል በመሠዊያው በኩል በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ዙሪያውን ተሰልፈው እንዲቆሙ አደረጋቸው።
ኢዩኤል 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ ከሌላው ጋር አይጋፋም፤ እያንዳንዱ መስመሩን አይለቅም፤ የጠላትን መሣሪያ ደምስሰው ያልፋሉ፤ ምንም የሚያግዳቸው የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መሥመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በጦር መሣርያ መካከል ያልፋሉ፥ የሚያስቆማቸው ነገር የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱ ከሌላው ርቆ አይቆምም፤ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ይሮጣሉ፤ በመሣሪያቸው ላይ ይወድቃሉ፤ እነርሱም አይጠፉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም። |
ሰይፋቸውን በእጃቸው ያያዙትን ጭፍሮች ሁሉ ንጉሡን ከአደጋ ለመከላከል በመሠዊያው በኩል በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ዙሪያውን ተሰልፈው እንዲቆሙ አደረጋቸው።
ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ።
ቅጽሩን የሚሠሩትን ሁሉ ያበረታቱ ነበር፤ ሌላው ቀርቶ፥ ተሸካሚዎቹ ጭምር በአንድ እጃቸው ሲሠሩ፥ በሌላ እጃቸው የጦር መሣሪያ ይዘው ለመከላከል ዝግጁዎች ነበሩ።
እኔም ሆንኩ የሥራ ጓደኞቼ፥ አገልጋዮቼም ሆኑ የክብር ዘቦቼ፥ ሁላችንም ሌሊት እንኳ ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። በዚህም ዐይነት ውሃ ስንቀዳ እንኳ መሣሪያችን ከእጃችን አልተለየም።