Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዩኤል 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አንዱ ከሌ​ላው ርቆ አይ​ቆ​ምም፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ይሮ​ጣሉ፤ በመ​ሣ​ሪ​ያ​ቸው ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እነ​ር​ሱም አይ​ጠ​ፉም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መሥመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በጦር መሣርያ መካከል ያልፋሉ፥ የሚያስቆማቸው ነገር የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንዱ ከሌላው ጋር አይጋፋም፤ እያንዳንዱ መስመሩን አይለቅም፤ የጠላትን መሣሪያ ደምስሰው ያልፋሉ፤ ምንም የሚያግዳቸው የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 2:8
11 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን በእጁ እየ​ያዘ በን​ጉሡ ዙሪያ ከቤተ መቅ​ደሱ ቀኝ እስከ ቤተ መቅ​ደሱ ግራ ድረስ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ቅ​ደሱ አጠ​ገብ እን​ዲ​ቆም አደ​ረገ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።


ቅጥ​ሩ​ንም የሚ​ሠ​ሩ​ትና ሸክም ተሸ​ካ​ሚ​ዎቹ በአ​ንድ እጃ​ቸው ይሠሩ ነበር፤ በአ​ንድ እጃ​ቸ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይይዙ ነበር።


እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።


ነፍ​ሱን ከሞት ያድ​ና​ታል፤ በሰ​ይ​ፍም እን​ዳ​ይ​ጠፋ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል።


ኃጥ​ኣ​ንን ግን አያ​ድ​ና​ቸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያዩ ዘንድ አይ​ወ​ዱ​ምና፥ ሲገ​ሥ​ፃ​ቸ​ውም አይ​ሰ​ሙ​ምና።


መን​ገ​ድ​ሽም ሮማ​ንና የተ​መ​ረጠ ፍሬ፥ ቆዕ ከና​ር​ዶስ ጋር ያለ​በት ገነት ነው፥


አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙ​ምም፤ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ አይ​ተ​ኙም፤ የወ​ገ​ባ​ቸ​ውን መታ​ጠ​ቂያ አይ​ፈ​ቱም፤ የጫ​ማ​ቸ​ውም ማዘ​ቢያ አይ​በ​ጠ​ስም።


እንደ ተዋ​ጊ​ዎች ይሮ​ጣሉ፤ እንደ ጦረ​ኞ​ችም በቅ​ጥሩ ላይ ይወ​ጣሉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በመ​ን​ገዱ ላይ ይራ​መ​ዳል፤ ከእ​ር​ም​ጃ​ቸ​ውም አያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉም።


ከተ​ሞ​ችን ይይ​ዛሉ፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ ይሮ​ጣሉ፤ ወደ ቤቶ​ችም ይወ​ጣሉ፤ እንደ ሌባም በመ​ስ​ኮ​ቶች ይገ​ባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos