ኢዩኤል 2:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሰማይና በምድር፥ ድንቅ ነገሮችን አሳያለሁ፤ ደምና እሳት፥ የጢስ ዐምድም ይታያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንቆችን በሰማያት፣ እንዲሁም በምድር፣ ደምና እሳት፣ የጢስም ዐምድ አሳያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፤ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። |
ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
የዐይ ከተማ ሰዎችም ወደ ኋላ መለስ ብለው ባዩ ጊዜ የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ የሸሹት እስራኤላውያን በአሳዳጆቻቸው ላይ ስለ ተመለሱባቸው፥ በየትም በኩል ለማምለጥ አልቻሉም።
የመጀመሪያው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በረዶና ደም የተቀላቀለበት እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድር ሢሶ ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሢሶ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣርም ሁሉ ተቃጠለ።
ሸምቀው የነበሩት ሰዎች በከተማው ብዙ የጢስ ደመና እንዲያስነሡ በዋናው የእስራኤል ሠራዊትና ሸምቀው በነበሩት ሰዎች መካከል የምልክት ስምምነት ተደርጎ ነበር።
ከዚህም በኋላ ምልክቱ ታየ፤ ይኸውም ጢሱ እንደ ደመና ሆኖ እየተትጐለጐለ ወደ ላይ ይወጣ ነበር፤ ብንያማውያንም ወደኋላቸው ሲመለከቱ ከተማይቱ በሙሉ በእሳት ተያይዛ ነበልባሉ ወደ ላይ ሲወጣ አዩ፤