ኢዩኤል 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እጮኛዋ ስለ ሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ልጃገረድ እናንተም አልቅሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅነት ዕጮኛዋን እንዳጣች ድንግል፣ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጮኛዋ ስለሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ልጅነት ባልዋ ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቍንጅናዋ ባል ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። |
እስከ አሁን ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ሆናችሁ በመቀማጠል ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን በፍርሃት ተንቀጥቀጡ! ልብሳችሁን አውልቃችሁ በወገባችሁ ላይ ማቅ ታጠቁ!
ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል።
የዓመት በዓል ደስታችሁን ወደ ሐዘን፥ ዘፈናችሁንም ወደ ለቅሶ እለውጠዋለሁ፤ አንድ ብቻ የሆነ ልጃቸው ሞቶባቸው እንደሚያለቅሱ ወላጆች ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ ማቅ እንድትለብሱ አደርጋለሁ፤ የዚያ ቀን ፍጻሜ የመረረ ይሆናል።
ታዲያ እግዚአብሔር እናንተና ሚስቶቻችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ እንዲኖራችሁ አድርጎ አልነበረምን? በዚህስ የእርሱ ዓላማ ምን ነበር? ዋና ዓላማው የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሆኑ ልጆችን እንድትወልዱ በመፈለግ ነበር፤ ስለዚህ ከእናንተ እያንዳንዱ ለሚስቱ የገባውን ቃል ኪዳን አያፍርስ።