አሁን ግን ከሞተ በኋላ ስለምን እጾማለሁ? ሕፃኑን እንደገና በሕይወት እንዲኖር ማድረግ ይቻለኛልን? እኔ አንድ ቀን ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ ተመልሶ አይመጣም።”
ኢዮብ 7:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ ሁሉ፥ ሞቶ ወደ ሙታን ዓለም የሚሄድ ሰው ተመልሶ አይመጣም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመና በንኖ እንደሚጠፋ፣ ወደ መቃብር የሚወርድም አይመለስም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመና ከሰማይ ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ ወደ መቃብር የሚወርድ ሰው ዳግመኛ አይወጣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም። |
አሁን ግን ከሞተ በኋላ ስለምን እጾማለሁ? ሕፃኑን እንደገና በሕይወት እንዲኖር ማድረግ ይቻለኛልን? እኔ አንድ ቀን ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ ተመልሶ አይመጣም።”
እኛ ሁላችን መሞታችን የማይቀር ነው፤ እኛ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር ግን በስደት ላይ የሚገኝ ሰው ከእርሱ እንደ ራቀ እንዳይቀር የሚመለስበትን መንገድ ያዘጋጅለታል እንጂ ሕይወቱ በከንቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።