በእኔ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ዘወትር ታገኛለህ፤ በእኔ ላይ የምታሳየው ቊጣ እያደገ ይሄዳል፤ እኔን ለማጥቃት ዘወትር አዳዲስ ዕቅዶችን እንደ ሠራዊት ታሰልፍብኛለህ።
ኢዮብ 7:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ እንደ ግዳጅ ሠራተኞች አይደሉምን? ቀኖቻቸው እንደ ቅጥር ሠራተኞች ቀኖች አይደሉምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ተጋድሎ አይደለምን? ዘመኑስ እንደ ምንደኛ ዘመን አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጥንቱን በምድር ላይ የሰው ሕይወት ጥላ አይደለምን? ኑሮውስ እንደ ቀን ምንደኛ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ወራቱም እንደ ምንደኛ ወራት አይደለምን? |
በእኔ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች ዘወትር ታገኛለህ፤ በእኔ ላይ የምታሳየው ቊጣ እያደገ ይሄዳል፤ እኔን ለማጥቃት ዘወትር አዳዲስ ዕቅዶችን እንደ ሠራዊት ታሰልፍብኛለህ።
የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም።
አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሠራተኞች የሥራ ውል እንደሚያልቅ ልክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር ነገዶች ክብር ይወገዳል፤
“ወደ ሕዝቅያስ ሄደህ እንዲህ በለው፤ ‘እነሆ፥ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እኔ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፤ እንባህንም አይቼአለሁ፤ ስለዚህም በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ፤
የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።”
ይህም በሚሆንበት ጊዜ ከገዛው ሰው ጋር ይመካከር፤ ዘመኑንም እርሱ ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቊጠሩት፤ ስለ እርሱም ነጻ መለቀቅ ተገቢውን ዋጋ በእነዚያ ዓመቶች ውስጥ ተቀጥሮ በሚሠራ ሰው ልክ ይተምኑት።
እርሱንም ነጻ ባወጣኸው ጊዜ አንድ ተቀጣሪ ለስድስት ዓመት ከሚሰጥህ እጥፍ አገልግሎት ስለ ሰጠህ ቅር አይበልህ። እንግዲህ ይህን አድርግ፤ እግዚአብሔርም በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።