ኢዮብ 41:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆዳውን በፈለግህበት ቦታ በጦር መብሳት፥ ጭንቅላቱንም በሾተል ወግተህ መሰንጠቅ ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳው ላይ ዐንካሴ ልትሰካ፣ ጭንቅላቱንም በዓሣ መውጊያ ጦር ልትበሳ ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጀርባው ቆዳዎች ጠንካራ ናቸው፤ አቤት ኩራት! በጥብቅ ማተሚያ እንደ ታተሙ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳቸው የተጣበቁ ናቸውና፥ ነፋስም በመካከላቸው መግባት አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅርፊቶቹ ጠንካራ ስለ ሆኑ እርሱ ትዕቢተኛ ነው፥ በጠባብ ማተሚያ እንደ ታተሙ ናቸው። |
ከቻልክ እስቲ እጅህን በላዩ ላይ አሳርፍበት። ከእርሱ ጋር የምታደርገውን ትግል በፍጹም አትረሳውም፤ ዳግመኛም ከእርሱ ጋር ለመታገል አትሞክርም።