ኢዮብ 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! አንድ ሰው ደፍሮ ቢናገርህ በትዕግሥት ታዳምጣለህን? ነገር ግን ከመናገር ማን ይቈጠባል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ከአንተ ጋራ ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን? ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር ትቀየማለህን? ቃልንስ ከመናገር ማን ሊቀር ይችላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመከራ ሳለህ ነገር አታብዛ፥ የነገር ብዛት ምን ይጠቅምሃል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰው ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ ቢሞክር ትቀይማለህን? ቃልንስ ከመናገር ሊቀር የሚችል ማን ነው? |
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።
ጌታ ሆይ! አንተ በእነርሱ ላይ ያለህ ቊጣ በእኔም ውስጥ ይነዳል። ከቶም ልታገሠው አልችልም።” እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “ቊጣዬን በመንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናትና በተሰበሰቡ ወጣቶች ላይ አፍስሰው፤ ባልና ሚስት በአንድነት ይወሰዳሉ፤ በዕድሜ ለገፉ ሽማግሌዎች እንኳ ምሕረት አይደረግላቸውም።”