ዳዊትም እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ ሕዝቡ እንዲቈጠር ትእዛዝ ያስተላለፍኩትም እኔ ነኝ፤ ታዲያ እነዚህ አሳዛኝ ሕዝብህ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔንና ቤተሰቤን ቅጣ እንጂ በሕዝብህ ላይ ይህንን መቅሠፍት አታውርድ።”
ኢዮብ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ በመላ ሰውነቱ ላይ ጒዳት ብታደርስበት በእርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪ እጅህን ዘርግተህ ዐጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፤ በርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፤ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳብስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል አለው። |
ዳዊትም እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ ሕዝቡ እንዲቈጠር ትእዛዝ ያስተላለፍኩትም እኔ ነኝ፤ ታዲያ እነዚህ አሳዛኝ ሕዝብህ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔንና ቤተሰቤን ቅጣ እንጂ በሕዝብህ ላይ ይህንን መቅሠፍት አታውርድ።”
እግዚአብሔርም ሰይጣንን “እሺ፤ እንግዲያውስ በኢዮብ ላይ ብቻ አንዳች ጒዳት አታድርስበት እንጂ ባለው ሀብት ሁሉ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ” አለው። ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።
የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።
ሕዝቡ ተስፋ ቈርጠውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ከመራባቸው የተነሣ ተበሳጭተው ወደ ሰማይ እያንጋጠጡ ንጉሣቸውንና አማልክታቸውን ይራገማሉ።
የእስራኤላዊቱ ልጅ የእግዚአብሔርን ስም ስለ ተሳደበ ወደ ሙሴ አቀረቡት፤ የእናቱም ስም ሰሎሚት የምትባልና ከዳን ነገድ የሆነው የዲብሪ ልጅ ነበረች።
ከዚህ በኋላ አንድ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “እነሆ አዳኝነት፥ ኀይል፥ መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል! ሥልጣንም የመሲሑ ሆኖአል! ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ሲያሳጣቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል፤