ኢዮብ 12:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እኔም የእናንተን ያኽል ማስተዋል አለኝ፤ ከቶ ከእናንተ በምንም አላንስም፤ እናንተ የተናገራችሁትን ሰው ሁሉ ያውቀዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ ከእናንተ አላንስም፤ እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ ማስተዋል እችላለሁ፥ ከእናንተም አላንስም፥ እንደዚህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ልብ አለኝ። እኔ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም፥ እንደዚህ ያለውን ነገር የሚያውቅ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ማስተዋል አለኝ፥ ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፥ እንደዚህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው? |