ኢዮብ 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያኽል ማስጨነቅህ አግባብ ነውን? አንተ ራስህ የፈጠርከውን ሰው መናቅ ይገባሃልን? የክፉ ሰዎችስ ሤራ ደስ ያሰኝሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣ እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣ የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የክፉዎችንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢኣተኛ ብሆን በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? የእጅህን ሥራ ቸል ብለሃልና፤ የኃጥኣንንም ምክር ተመልክተሃልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የኃጥአንንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? |
“ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”