ኤርምያስ 8:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “እነሆ የመከር ወራት አለፈ፤ በጋውም ተፈጸመ፤ እኛ ግን አልዳንም!” በማለት ይጮኻሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መከሩ አልፎአል፥ በጋው ተፈጽሟል፥ እኛም አልዳንም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከሩ አልፎአል፤ በጋውም ዐልቋል፤ እኛም አልዳንንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም። |
እስቲ አድምጡ! “እግዚአብሔር ዳግመኛ በጽዮን አይገኝምን? የጽዮን ንጉሥ ዳግመኛ በዚያ አይኖርምን?” እያሉ ሕዝቤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ሲጮኹ እሰማለሁ። ንጉሣቸው እግዚአብሔርም፦ “ጣዖቶቻችሁን በማምለክና ለባዕድ አማልክታችሁም በመስገድ የምታስቈጡኝ ስለምንድን ነው?” ሲል ይመልስላቸዋል፤
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።
አንቺንና በውስጥሽ ያሉትንም ልጆችሽን በመሬት ላይ ጥለው ያወድማሉ፤ ሳይፈርስ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ በቦታው አይተዉልሽም፤ ይህም የሚሆነው፥ እግዚአብሔር አንቺን ሊያድን የመጣበትን ጊዜ ባለማወቅሽ ነው።”