አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤ እንስሶች በመሠዊያ ላይ እንዲቃጠሉ፥ ወይም ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፤ በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደረግኸኝ።
ኤርምያስ 7:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸውም ጊዜ ስለሚቃጠልም ሆነ ስለ ሌላው ዐይነት መሥዋዕት ምንም ትእዛዝ አልሰጠኋቸውም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ፣ ስለ መሥዋዕቶችና ስለሚቃጠል መሥዋዕት አልተናገርኋቸውም፤ ትእዛዝም አልሰጠኋቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ቀን ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት ለአባቶቻችሁ አልተናገርሁምና፥ አላዘዝኋቸውምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ቀን ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ቍርባን ለአባቶቻችሁ አልተናገርሁምና፥ አላዘዝኋቸውምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ቀን ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት ለአባቶቻችሁ አልተናገርሁምና፥ አላዘዝኋቸውምም። |
አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤ እንስሶች በመሠዊያ ላይ እንዲቃጠሉ፥ ወይም ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፤ በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደረግኸኝ።
የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከክፉ አድራጎት በስተቀር ምንም ያደረጉት መልካም ነገር የለም። በተለየም የእስራኤል ሕዝብ በእጃቸው በሠሩት ጣዖት እኔን ከማስቈጣት በቀር ምንም የሠሩት ነገር የለም።
ሂዱ፤ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’ ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት እንደ ሆነ መርምራችሁ አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት ነው” አላቸው።
ስለዚህ ሰው በፍጹም ልቡ፥ [በፍጹም ነፍሱ፥] በፍጹም ሐሳቡ፥ በፍጹም ኀይሉ እግዚአብሔርን መውደድ ይገባዋል፤ እንዲሁም ጐረቤትን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከማቅረብ ይልቅ እነዚህን ሁለቱን ትእዛዞች መጠበቅ ይበልጣል።”
ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚወደው የቱን ይመስልሃል? መታዘዝን ወይስ ቊርባንና መሥዋዕት ማቅረብን? ለእርሱ መታዘዝ ምርጥ የበግ መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤