ኤርምያስ 51:61 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራያንም እንዲህ አልኩት “ባቢሎን እንደ ደረስህ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ለሕዝቡ አንብብላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፤ “ባቢሎን በደረስህ ጊዜ፣ ይህን ቃል ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማንበብ አትዘንጋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፦ “ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ልብ ብለህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፥ “ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ እይ፤ ይህንም ቃል ሁሉ አንብብና፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፦ ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ እይ፥ ይህንም ቃል ሁሉ አንብብና፦ |
ከዚያም በኋላ ‘ጌታ ሆይ! አንተ ይህን ስፍራ እንደምታጠፋ ተናግረሃል፤ ስለዚህም ሕይወት ያለው ተንቀሳቃሽ ፍጥረት አይኖርባትም፤ ሰውም እንስሳም ስለሚጠፋ ለዘለዓለም ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች’ በል።
ይህችን መልእክት እናንተ ካነበባችኋት በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።
ይህ ሁሉ የሚፈጸምበት ጊዜ ቅርብ ስለ ሆነ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው! እንዲሁም የትንቢቱን ቃል የሚሰሙና በትንቢቱም ውስጥ የተጻፈውን የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።