ኤርምያስ 51:52 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ ጣዖቶቿን የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምድሯም ሁሉ፤ ቍስለኞች ያቃስታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምቀጣበት በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጋው የሚያቃስትበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጉት ያንቋርራሉ። |
ስለዚህም የባቢሎንን ጣዖቶች የማስወግድበት ጊዜ ይመጣል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ኀፍረት ይደርሳል፤ የተገደሉባት ልጆችዋ ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
መቅሠፍቴን በእናንተ ላይ አመጣለሁ፤ በየመንገዱም ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ በየአቅጣጫው በሚነሣባችሁ ጦርነት ምክንያት በመካከላችሁ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሕዝቦችም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
በዚህም ዐይነት የባቢሎንን ንጉሥ ኀይል በማጠንከር የእኔን ሰይፍ በእጁ አስይዘዋለሁ። የግብጽን ንጉሥ ኀይል ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ደረሰበት ሰው በጠላቱ ፊት ይቃትታል።